የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ከተማሪዎች አገልግሎት ዲን ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የሁሉንም ካምፓሶች የተማሪዎች ህብረት አባላት እና የዩኒቨርሲቲውን አመራሮች የትዉዉቅ መድረክ የካቲት 14/2017 ዓም በዋናው ግቢ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ አካሂዷል::
በትውውቅ መድረኩ ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ: የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ: የተማሪዎች አገልግሎት ዲን ዶ/ር አመሎ ሶጌ እንዲሁም የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ እሴይ ጴጥሮስ ንግግር አድርገዋል::

ተማሪ እሴይ ጴጥሮስ ስለ መድረኩ ዓላማ ሲያብራራ የዩኒቨርሲቲውን ከፍተኛ አመራር በሰባቱም ግቢዎች ከሚገኙት የተማሪ መማክርት አባላት ጋር ለማቀራረብና አሁናዊ የተማሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ የሚታዩትን ችግሮች እንዲሁም የማሻሻያ እርምጃዎች በተመለከተ በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ፊት ለፊት ቀርቦ ለመነጋገር ብሎም በቅርበት ለመስራት እንድያመች ለማድረግ መሆኑን ገልፅዋል::
የተማሪዎች ካውንስል አባላትም ለአመራሮች በርካታ ጥያቄዎችን አንስተው የተወያዩ ሲሆን የተማሪዎችን አገልግሎት አሰጣጥ ለማስተካከል ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋና ለመግለፅ እና እንኳን ደህና መጡ በማለት ለፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ልዩ ስጦታ አበርክተውላቸዋል::
ክቡር ፕሬዝዳንቱም ለተማሪ ተወካዮች በትምህርት ጥራት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በጋራ እየተናበቡ እንደሚሰሩ ቃል ገብተው ተማሪዎችም እንደ ሀገር ተስፋ ሰጥተዉ መጪው ግዜ የተሻለ እንዲሆን በኃላፊነት ስሜት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እና የወከሉትን ተማሪም በታማኝነት እንዲያገለግሉ ምክርና መመሪያ ሰጥተዋል:።
