Skip to Content

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ 214 የሕክምና ባለሙያዎችን አስመረቀ

የካቲት 15 ቀን 2017 ዓም ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ 214 የሕክምና ባለሙያዎችን አስመረቀ::

 

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመጀመሪያ ዲግሪ መርሃግብር በሰባት ትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን 214 የሕክምና ባለሙያዎች ለ19ኛ ግዜ በደማቅ ስነስርዓት አስመረቋል::


የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሁሉም የትምህርት ዘርፎች ብቁ ባለሙያዎችን የማፍራት ሀገራዊ ግዴታውን በስኬታማነት እየተወጣ እንደሚገኝ የገለጹት ፕሬዚደንት ዶ/ር ችሮታው አየለ "በሀገራችን ከፍተኛ የባለሙያ እጥረት በሚታይበት የጤና ሳይንስ ዘርፍ ትምህርታችሁን ያጠናቀቃችሁ የዛሬ ተመራቂዎች በቀጣይ በምትሄዱበት የስራ አለም ችግር ፈቺ መፍትሔ በማፍለቅ የጤና ዘርፉ ላይ መልካም አሻራችሁን በማሳረፍ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አምባሳደር መሆን ይጠበቅባችኋል" ብለዋል።



በኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ት/ት፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚና የዕለቱ የክብር እንግዳ ዶ/ር ሰራዊት ሀንዲሶ የጤና ሳይንስ ትምህርት የሚጠይቀውን ከፍተኛ ትጋት ተቋቁመው ለዚህች ቀን ለደረሱት ተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የገበዩትን እውቀት ተጠቅመው የሀገራችንን የጤና ስርአት ለማዘመንና እየተሰራ ባለው ስራ ላይ በታማኝነትና በላቀ ብቃት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አደራ ብለዋል።


የኮሌጁ ቺ/ኤክ/ዳይሬክተር ዶ/ር አለሙ ጣሚሶ በበኩላቸው ኮሌጁ የተማረ የሰው ሀይል ከማፍራት በተጨማሪ በኮምፕሪሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታሉ አማካኝነት በዓመት ከ20 ሚሊዮን በላይ ለሚጠጉ የህብረተሰብ ክፍሎች በየጊዜው እየሰፋ የመጣውን የህክምና አገልግሎት በማቅረብ ድርብ ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

Share this post
Tags
Archive
Ambassador of Czech Republic to Ethiopia visits HU with leaders of MU