Skip to Content

በባዮቻር (Biochar) አመራረትና ጥቅሞቹ ላይ ለአርሶ አደሮች ስልጠና ተሰጠ።

ጥር 10 ቀን 2018 ዓ/ም

በሀዋሳ ዩኒቨረሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ የማህበረሰብ አገልግሎት ክፍል በሲዳማ ብ/ክ/መ/ዳሌ ወረዳ በሾዬ ቀበሌ ለሚገኙ አርሶ አደሮች “የተቀናጀ የተረፈ ምርት አወጋገድ ቴክኖሎጂ፡ የቡና አሸራን በመጠቀም ባዮቻርና የተፈጥሮ ማዳበርያ በማምረት የአፈር ጤንነትን መጠበቅ፣ ዘላቂ የግብርና ምርትን ማረጋገጥ“ በሚል መሪ ሃሳብ የግንዛቤ ማስጨበጫና የተግባር ስልጠና በገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ተሰጥቷል።

ፕሮግራሙን የሚያስተባብሩት የኮሌጁ መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር ክብረስላሴ ዳንኤል እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲ ከሚያተኩርባቸው ስራዎች መካከል የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ የምርምር ስራዎችን መስራትና የጥናት ውጤቱን ተከትሎ የሚመነጩ የፈጠራና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ማስተዋወቅ አንዱ መሆኑን ጠቁመው በሲዳማ ክልእ በሚገኙ አርሶአደሮች ዘንድ በብዛት የሚመረተውን ቡና ውጋጅ በቴክኖሎጂ ታግዞ የአፈር ለምነት ለመጨመር፣ ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል፣ አከባቢው ለህብረተሰቡ ጤና ምቹ እንዲሆን ለማስቻል ባዮቻር ማዘጋጀት መቻሉን ገልፀዋል።


ባዮቻር (የተረፈ ምርት ከሰል) ማምረት የአፈር ለምነትንና ምርታማነትን ከማሻሻል ባሻገር የአየር ንብረት ለውጥን ተፅዕኖ ከመቀነስ አንጻር አይነተኛ ሚና እንዳለው የገለፁት መምህር ተፈሪ ሻንካ ከዚህ ቀደም ምርታማነትን የሚያሻሽሉ የምርምር ውጤቶችን ከመቀበል አኳያ በአርሶአደሩ ላይ ይታይ የነበረው የአመለካከት ክፍተት መሻሻል ማሳየቱን ተናግረዋል።

Share this post
Tags
Archive
የማህበራዊ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ አንደኛ ደረጃ ማግኘቱን አስመልከቶ ልዩ ፕሮግራም አካሂዷል።