Skip to Content

በHETRIIL አዋጅ መተግበርያ እና የኢንዱስትሪ ተቋማት ጥናት ላይ ስልጠና ተሰጠ።

ጥር 7/2018 ዓ/ም


የትምህርት ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ እና ከፍተኛ ትምህርት እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ትስስርን ለማጠናከር ባጸደቀው የHETRILL አዋጅ መሰረት በሀገርአቀፍ ደረጃ ከተደራጁት ስድስት የማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች አንዱ ሆኖ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚመራውና 10 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በስሩ በያዘው የደቡብ ክላስተር ስር ለሚገኙ ተቋማት ፎረም ላይ በአዋጁ መተግበርያ ሲስተም አሰራር እና የኢንዱስትሪ ዳሰሳ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።


በትምህርት ሚኒስቴር የተቋማት ትስስር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ዛይድ አባዲ እንደተናገሩት ስልጠናው በአዋጁ ስር የወጡ 7 መመሪያዎችን መሰረት በማድረግ የኢንዱስትሪ-ዩኒቨርሲቲ-ቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት-የምርምር ተቋማት ትስስርን (HETRIIL) ለማጠናከር በየክላስተሩ የሚገኙ ተቋማት በአካባቢዎቻቸው የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ያላቸውን አቅምና እድል የዳሰሰ ጥናት በማድረግ ውጤቱን መሰረት ያደረገ የማጓደን (mapping) ስራ መስራት የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መሆኑን አስረድተዋል:: በተጨማሪም በHETRILL ዲጂታል ሶፍትዌር አጠቃቀም ላይ የተሻለ መረዳትን የሚፈጥር መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።


የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ትብብር ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ታፈሰ ማቴዎስ በበኩላቸው የአንድ ሀገር እድገት ከሚረጋገጥባቸውና ከሚጸናባቸው አስፈላጊ ቁልፍ ነገሮች መካከል ለምርምርና ፈጠራ የሚሰጠው ቦታ አንዱ መሆኑን ጠቁመው ይህንን የምርምርና የፈጠራ ስራ የሚሰሩ ተቋማት ደግሞ ዘርፈ-ብዙ በመሆናቸው ተቋማቱን የሚያስተሳስርና በቅንጅት የሚያሰራ መመሪያ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተዘጋጅቶ በስድስት ክላስተሮች መደራጀቱን ተናግረዋል። ዶ/ር ታፈሰ አክለውም የተቋማቱን ትስስር ውጤታማ ለማድረግ የኢንዱስትሪ ተቋማትን ሁኔታ የዳሰሰ ጥናት ማድረግ (Industry mapping) አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ረገድ የሚሰራው ስራ የረጅም ጊዜ ተጽዕኖ ስለሚኖረው ወደስራ ከመገባቱ በፊት በሁሉም ባለድርሻ አካላት ዘንድ የጋራ ግንዛቤ ሊያዝበት ይገባል ብለዋል።

Share this post
Tags
Archive
በባዮቻር (Biochar) አመራረትና ጥቅሞቹ ላይ ለአርሶ አደሮች ስልጠና ተሰጠ።