Skip to Content

የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ተማሪዎች ማኅበር (JCSA) 129ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አክብሯል።

የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ተማሪዎች ማኅበር (JCSA) 129ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አክብሯል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ተማሪዎች ማኅበር (JCSA) 129ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አባት አርበኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አክብሯል።


ዓድዋንና ኢትዮጵያን የተመለከቱ ተውኔት፣ ፉከራና ሽለላ፣ ዲስኩር፣ ሙዚቃ፣ ከክብር እንግዶች ጋር የተደረጉ ቆይታዎችና መልዕክቶች የዝግጅቱ አካል ነበሩ። 

የማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ፕ/ር ዘለቀ አርፍጮ የዓድዋ ድል መታሰቢያ በነጻነትና በኩራት እንድንኖር ያስቻሉን ጀግኖች አባቶቻችንን የምናመሠግንበት መሆኑን አንስተው ይህ ትውልድም በተሰማራበት ዘርፍ የራሱን አኩሪ ገድል ለመፈጸም በቁጭት የሚነሳበት ሊሆን ይገባል ብለዋል።


የዝግጅቱ የክብር እንግዳ ከነበሩት መካከል በተለያዩ ዓውደ ውጊያዎች በመሠለፍ ሀገራቸውን ከጠላት የጠበቁና ድል ያደረጉት ሻለቃ ጳውሎስ ጌታቸው ባስተላለፉት መልዕከት የዓድዋ ድል ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ልዩ ስፍራ እንዲኖራት ያስቻለና በውድ ልጆቿ መስዋዕትነት የተገኘ መሆኑን አንስተው ትውልዱ በአግባቡ ሊዘክረው ይገባል ብለዋል።

የዓድዋ ድል ትልቁ ምስጢር አንድነት እንደነበርና የአሁኑ ትውልድም ከጥላቻና መለያየት ይልቅ ፍቅርና አንድነት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባው የተናገሩት ደግሞ ሻምበል ሐብታሙ ገበየሁ ናቸው።


የግሎባል ፒስ ባንክ ስራ አስኪያጅ አቶ አርጋው አየለ፣ መምህር ከያኒና ሀያሲ ዘመዱ ደምስስ፣ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ አቶ ደያሞ ዳሌ እና መምህርና ጋዜጠኛ አሳምሬ ሳህሉም በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ዓድዋን የተመለከቱ አዝናኝና አስተማሪ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

Share this post
Tags
Archive
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመንገድ ትራፊክ አደጋና ደህንነት ላይ የባለድርሻ አካላት ውይይት አካሄደ።