በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በ2016 የበጀት አመት የተከናወኑ 8 የምርምር ስራዎችን ለመገምገም ያዘጋጀው ዓመታዊ የምርምር አውደጥናት የካቲት 20/2017 ዓም አካሂዷል።
የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ዙፋን በደዊ ፕሮግራሙን ሲያስጀምሩ እንደገለፁት የዲስፕሊነሪ ጥናቶች በአብዛኛው በአንድ አመት ጊዜ የሚጠናቀቁ በመሆኑ በየወቅቱ የሚገኙበትን ደረጃና ግኝቶቹን መገምገም በሲንየር እና ጀማሪ ተመራማሪዎች መካከል በምርምሩ ሂደት ላይ ከፍተኛ የልምድ ልውውጥና የማሻሻያ ግብዓቶችን ለማግኘት አዎንታዊ ሚና ይጫወታሉ። ዶ/ር ዙፋን አክለውም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ወደ ምርምር ዩኒቨርሲቲነት እያደረገው ባለው ሽግግር ምክንያት በቀጣይ በርካታ ተመራማሪዎችን የሚያሳትፈው ጨብጥ-ተኮር የምርምር ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራበት ተናግረዋል።

በ2016 ዓ.ም የተከናወኑ የዲሲፕሊነሪ የምርምር ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ጥራታቸውንና ደረጃቸው እንዲሁም ምን ያህል ችግር ፈቺ ናቸው የሚለውን በተመለከተ ግምገማ እንደተደረገባቸው የገለፁት የኮሌጁ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተባባሪ ዲን ዶ/ር ከድር ወልይ የምርምር ስራዎቹ በሚያስመዘገቡት የግምገማ ደረጃ መሰረት ውጤት እንደሚሰጣቸውና በቀጣይ ማሻሻያዎችን የሚያደርጉበት ድጋፍና ክትትል እንደሚዘጋጅ ተናግረዋል።
