Skip to Content

ለኮሌጁ መምህራን በግራንት ፕሮፖዛል አጻጻፍ ላይ ስልጠና ተሰጠ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና ተመራማሪዎች ከአሜሪካው Thaddeus Stevens College of Technology በፉልብራይት ስኮላርሽፕ ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመጡት ፕሮፌሰር ናስር ቦጋለ አማካኝነት በግራንት ፕሮፖዛል አጻጻፍ ስነ-ዘዴ ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።


የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ዙፋን በደዊ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት የኮሌጁ መምህራን የመማር ማስተማርና የምርምር ስራዎችን ሲሰሩ  መቆየታቸውን አንስተው በዩኒቨርሲቲው በተቀመጠው የልየታ አቅጣጫ መሰረት ሁሉም አካዳሚክ ሰራተኛ በራሱ ምክረሀሳብ አዘጋጅቶ የምርምር ፈንድ የሚያፈላልግበትና ምርምሮችን የሚሰራበት አሰራር የመዘርጋት እንቅስቃሴዎች በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል።



ተመራማሪዎች የምርምር ምክረሃሳቦቻቸውን አሳማኝ በሆነ መንገድ ለሀገር ውስጥ እንዲሁም ለአለምአቀፍ ፈንድ አቅራቢ ተቋማት ማቅረብና ማሸነፍ እንዲችሉ መሰል ስልጠናዎች የላቀ ሚና እንደሚጫወቱ የገለጹት ዶ/ር ዙፋን በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባካበቱት ፕሮፌሰር ናስር ከሚሰጠው ስልጠናና ተሞክሮ በኃላ በኮሌጁ የምርምር ስራዎች ብዛትና ጥራት ላይ መሻሻል ይመጣል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።


ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የምርምር ስራዎችን የማከናወን ግዴታ ቢኖርባቸውም እንደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያሉ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በዚህ ረገድ መሪ ሆነው በመውጣት ምሳሌ ለመሆን እየሰሩ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የኮሌጁ የም/ቴ/ ሽግግር ተባባሪ ዲን ዶ/ር ከድር ወልይ ሲሆኑ ስልጠናው የተዘጋጀው ይህንን ግብ ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ አብራርተዋል።

Share this post
Tags
Archive
የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ተማሪዎች ማኅበር (JCSA) 129ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አክብሯል።