Skip to Content

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከሲዳማ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ጋር ሶፍትዌር ለማበልፀግ ውል ተፈራረመ።

ህሳስ 10/2018 ዓ/ም

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የሰው ሃብት አስተዳደር ሥርዓቱን ዲጂታል ለማድረግ የሚረዳው የሶፍትዌር ሲስተም እንዲሰራለት የሥራ ውል ስምምነት ተፈራርሟል።


የፐብሊክ ሰ/ሰ/ሃ/ል/ቢሮ ኃላፊ አቶ መንግስቱ ማቴዎስ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት የሰራተኞች ቅጥር እና አጠቃላይ መረጃ አስተዳደር በዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ እና ከታችኛው የሥራ መዋቅር ጀምሮ ያለውን የክልሉን ሰራተኞች ሙሉ መረጃ ለማስተዳደር በአሁኑ ሰዓት ክልሉ በተጨባጭ ካጋጠመው ችግር ተነስቶ ዩኒቨርሲቲው እንዲረዳው መፈለጉን ገልፀዋል። ኃላፊው ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የክልሉን ማህበረሰብ ችግሮች ለመፍታት በጥናትና ምርምር የተደገፈ በርካታ ድጋፍ በየግዜው እንደሚያደርግ አስታውሰው መንግስት ለሰራተኛው በአጠቃላይ በቢሊዮን የሚቆጠር ብር የሚከፍል እንደመሆኑ በተዛባ መረጃ አያያዝ የተነሳ አላስፈላጊ ወጪ እና ከፍተኛ ብክነት እንዳለ ለማወቅ ችለናል እና ይሄንን በፍጥነት ለማስቀረት ዩኒቨርሲቲው ላይ እምነት አለን ብለዋል።


የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ በበኩላቸው መረጃ ማለት ትክክለኛ ተቋማዊ ውሳኔዎችን ለመወሰን ዋነኛው ግብዓት መሆኑን በመረዳት ክልሉ ለጠየቀን ትብብር ከልብ እናመሰግናለን ካሉ በኃላ የኛ ባለሙያዎች ይህንን ሲስተም በብቃት እንደሚያዳብሩት ያላቸውን እምነት ገልፀዋል:: ፕሬዝዳንቱ የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤትም አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እና ክትትል ለባለሙያዎች እንዲያደርግ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

Share this post
Tags
Archive
ኮሌጁ አለምአቀፉን የGIS ቀን አከበረ።