Skip to Content

በሲዳማ ክልል የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች አቅም ዳሰሳ እና የኢንዱስትሪ ዞኖች ልየታ ጥናት ላይ ውይይት ተካሄደ።

ታህሳስ 6/2018 ዓ/ም


በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከሲዳማ/ብ/ክ/መ/ኢንዱሰትሪ ልማት ቢሮ ጋር በመተባብርር በክልሉ የሚገኙ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች አቅም ዳሰሳ እና የኢንዱስትሪ ዞኖች ልየታ (clustering) ላይ የሚያካሂደው ጥናት ላይ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሂዷል።


የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ በምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በሀገራችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚገኙት በሲዳማ ክልል መሆኑ በራሱ ትልቅ ዕድል እንደሆነ ጠቅሰው በዩኒቨርሲቲው እንደ አጠቃላይም ሆነ በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ የሚገኙ ተመራማሪዎችና ምሁራን ይህንኑ እድል ምርምሮቻቸውን በቀላሉ ወደ ተግባር ለመለወጥ እንደ አመቺ ሁኔታ መጠቀም ይገባቸዋል ብለዋል።

የሲ/ብ/ክ/መ/ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ በበኩላቸው ኢንዱስትሪዎችን ከኢንስቲትዩቱ ጋር በምርምር አስተሳስሮ የመጓዙ አቅጣጫ የክልሉ ፕሬዚደንት በተገኙበት በውይይት እና በምክክር ዳብሮ በክልሉ 5 ዞኖችና 19 ወረዳዎች ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።


የክልሉን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አቅም ከሀገራዊ ደረጃዎች አንጻር የሚገኝበት ሁኔታ፣ ያሉ እድሎችና አቅሞች እንዲሁም ኢንዱስትሪዎችን በአቅራቢያው ካለው ሀብት ጋር በማስተሳሰር በሚሰራው የኢንዱስትሪ ዞን ልየታ ላይ ዶ/ር ኢ/ር ፋሲካ ቤተ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

Share this post
Tags
Archive
በዩኒቨርሲቲዉ ግቢዎች መካከል ሲካሄድ የቆየዉ ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ።